Besys Technology PLC logo

የቡና ማሸግ ሰራተኛ | Coffee Packaging Worker

Besys Technology PLC
17 days ago
Full-time
On-site
Bole Road Friendship Building 4th Floor #401 and 2nd Floor 211/2

Closing Date
2026/02/28 (estimated based on Feb 21, 2018 E.C.)

Reference Number
BST260219-CPW

Job Title
Coffee Packaging Worker (የቡና ማሸግ ሠራተኛ)

Job Category
Manufacturing / Production

Company
Besys Technology PLC

Job Type
Full Time

Location - Country
Ethiopia

Location - Province
Not Applicable

Location - Town / City
Addis Ababa (African Avenue)

የቢሲስ ቴክኖሎጂስ ሃ/የተ/የግ/ማ እህት ኩባንያ የሆነው ግዕዝ ኮፊ በሚከተሉት የስራ ዘርፎች ሰራተኞችን አወዳድሮ መቅጠር ይፈልጋል
የቡና አሻጊ ስራተኛ
ለቡና ማሸግ ስራ (Coffee Packaging) የወጣ የስራ ዝርዝር መግለጫ (Job Description)

የስራው መጠሪያ፡ የቡና ማሸግ ስራተኛ (Coffee Packaging Worker)
ብዛት፦ 2
የተቆላ ወይም የተቀጠቀጠ ቡናን በጥራት፣ በንፅህና እና በኩባንያው መመዘኛ መሠረት በመመዘን፣ በማሸግ እና ለገበያ ዝግጁ በማድረግ የሥራ ሂደቱን ማገዝ ነው።

ዋና ዋና ኃላፊነቶች (Key Responsibilities)፦
ቡናን መመዘንና መለካት፦ የታዘዘውን የቡና መጠን (ለምሳሌ፦ 250ግ፣ 500ግ፣ 1ኪሎ) በትክክል በመመዘን ወደ ማሸጊያ ከረጢቶች መገልበጥ።
በማሽን ማሸግ፦ የማሸጊያ ማሽኖችን በመጠቀም ከረጢቶችን በሙቀት መዝጋት (Sealing) እና አየር እንዳይገባ አድርጎ ማሸግ።
መለያ (Label) መለጠፍ፦ በእያንዳንዱ ፓኬት ላይ የምርት ስም፣ የጥራት ደረጃ፣ የምርትና የአገልግሎት ማብቂያ ቀን የያዙ መለያዎችን በትክክል መለጠፍ።
ጥራት መቆጣጠር፦ የታሸጉት ከረጢቶች የተቀደዱ ወይም ያልተገጠሙ አለመሆናቸውን ማረጋገጥ እና ንፅህናቸውን መጠበቅ።
በካርቶን ማደራጀት፦ የታሸጉትን ምርቶች በብዛት ወደ ትላልቅ ካርቶኖች በመደርደር ለሽያጭ ወይም ለኤክስፖርት ዝግጁ ማድረግ።
የስራ አካባቢ ንፅህና፦ የቡና ማሸጊያ ማሽኖችን እና የሥራ ቦታን ዘወትር በንፅህና መያዝ።

ተፈላጊ ችሎታዎች (Requirements)፦
ትኩረት መስጠት፦ በክብደትና በመለያዎች ላይ ስህተት እንዳይፈጠር ከፍተኛ ጥንቃቄ ማድረግ።
አካላዊ ብቃት፦ ለረጅም ሰዓታት ቆሞ ለመስራትና መጠነኛ ሸክሞችን ለማንቀሳቀስ የሚችል/ምትችል።
ታማኝነትና ስነ-ምግባር፦ የምርቱን ጥራትና የኩባንያውን ደንብ ጠብቆ የመስራት ዝንባሌ።
የትምህርት ደረጃ፦
ቢያንስ 8ኛ ወይም 10ኛ/12ኛ ክፍል ያጠናቀቀ (እንደ ተቋሙ ፍላጎት ሊለያይ ይችላል)።

የማመልከቻ ጊዜ፦

አመልካቾች እስከ መጋቢት 26, 2018 የትምህርት ማስረጃ ፤ ሲቪ እና የስራ ልምድ ከዚህ በታች በተቀመጠው አድራሻ ማስገባት ይኖርባቸዋል። 

 ለማመልከት 'Apply now' የሚለውን ይጫኑ👇🏾!