መስፈርቶች
-
የትምህርት ደረጃ፦ ቢያንስ የ8ኛ ክፍል ትምህርትን ያጠናቀቀች
-
የስራ ልምድ፦ በጽዳት ወይም በቢሮ ረዳትነት ስራ ላይ ልምድ ያላት ቢሆን ይመረጣል
-
ደመወዝ፦ በድርጅቱ ስኬል መሰረት
-
የስራ አይነት፦ ሙሉ ቀን
-
የስራ ቦታ፦ አዲስ አበባ
የስራው ማጠቃለያ
ቢሲስ ቴክኖሎጂስ ኃ.የተ.የግ.ማ (BESYS Technologies PLC) ታማኝ እና ታታሪ የሆነች የጽዳት እና የቢሮ ረዳት ይፈልጋል። ዋናው የስራው ዓላማ ቢሮው ንጹህ፣ የተደራጀ እና ለሰራተኞችም ሆነ ለእንግዶች ምቹ እንዲሆን ማድረግ ነው።
ዋና ዋና ተግባራት እና ኃላፊነቶች
- ቢሮዎችን፣ የስብሰባ አዳራሾችን፣ ኮሪደሮችን እና መጸዳጃ ቤቶችን በየቀኑ ማጽዳት
- የጽዳት እቃዎችን በአግባቡ መጠቀም እና ማስቀመጥ
- ለሰራተኞች እና ለእንግዶች ቡና፣ ሻይ እና ሌሎች መጠጦችን ማዘጋጀትና ማቅረብ
- የወጥ ቤት እና የቢሮ ቁሳቁሶችን ንጽህና መጠበቅ
- የታዘዙ ሌሎች ቀላል የቢሮ ስራዎችን ማገዝ
- የጽዳት ቁሳቁሶች ሲያልቁ መከታተል እና ሪፖርት ማድረግ
- ሁልጊዜም ቢሮው ንጹህ እና ስርአት ያለው መሆኑን ማረጋገጥ
ተፈላጊ ችሎታዎች እና ባህሪያት
- የግል ንጽህናን መጠበቅ እና ስርአት ያለው አለባበስ
- ሰዓት አክባሪነት እና ታማኝነት
- ትህትና እና ከሰው ጋር በጋራ የመስራት ችሎታ
- መመሪያዎችን በትክክል የመቀበል እና የመተግበር ብቃት
ለማመልከት 'Apply now' የሚለውን ይጫኑ👇🏾!